Ethiopian Empire
The Throne of Ethiopia is right; Eprp, Meison, Eprdf and Olf are simply wrong.
Posts  1 - 1  of  1
abbatobia1
ከተማሪው እንቅስቃሴ ጀምሮ እንደነ ኢሕአፓ , መኢሶን , ወያኔ , ኢሕአድግ , ኦነግ የመሳሰሉት , ዳግማዊ ዐጤ ምኒልክንና ነፍጠኛ ወታደሮቻቸውን , ደቡብ ኢትዮጵያን በሚመለክት , ተስፋፊ ቅኝ ገዢ , የሰው አገር ወራሪ እያሉ ሲጠሩ ከርመው ይኼው አሁን አንቀሥ 39 የመገንጠል መብት ላይ ደርሰናል . ምኒልክ ደሞ ጥንታዊ ግዛቴን ነው ያስመለስኩት ብለው ነግረውናል .

ምኒልክ ተነኩ ማለት ቤት ተነካ ማለት ሰለሆነ ይረብሸኛል . ታዲያ በዚሁ ምክንያት ሐቁን ፍለጋ ተሰማርቼ ከገለልተኛ የዓይን ምሥክሮች ያጠናቀርኩትን ዘገባ ለእያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ አቀርባለው . መረጃውን ያገኘሁባቸውን መጣሕፍታት ቅንፍ ውስጥ ይመልከቱ .

ከኦሮሞ ልጀምር -

1. እነዚህ ጋሎች ከአቢሲኒያ ችግሮች አንዱ ናችው . አገሪትዋን በ 16ኛው ክ /ዘመን ከየት እንደመጡ ሳይታውቅ በጥሰው ገብተው ቦታወችን በሚገባ ተቆጣጥረው በከፍተኛ ሁኔታ የዘውዱን አገር እናወጡት . በተለይ የንጉሡ እናት ሆን ብላ ልጅዋን ንጉሡን በ 18ኛው ክ /ዘመን ለጋላ ከዳረችው ጀምሮ የጋላ መላ ብልሹ በነበረው ፖለቲካ ሥርዐት ውስጥ ገብቶ ሁኔታዎች እንዲባባሱ አደረገ .

ጋላ የሚባለው ቃል ጋልኛ ሲሆን ትርጉሙም "ወራሪ ' ማለት ነው ይባላል . እስላሞች ደሞ ሌላ ትርጉም ይሰጡታል . ትርጉሙ "እምቢ አለ " በዐረብኛ ነው ("ጋ ላ ").

መሐመድ ለጋሎች አለቃ ሰው ልኮ እስልምናን ተቀበል ቢለው , አለቃው እምቢ ቢለው "ካሁን በኅዋላ የገብረኤልን ጥሪ አልቀበል ስላለ ዘርማ ዘሩ "ጋ ላ " መጠሪያው ይሁን ብሎ ተናገረ ይላሉ እስላሞቹ .

እነዚህ ጋሎችን ከሙሮች ጋር ማዛመድ ትልቅ ስህተት ነው . ሙሉ ለሙሉ የተለያዩ ዘሮች ናቸው .
(Views in Central Abyssinia, Sophie F. F. Veitch, 1868).

2. ጋሎች እንደ ማንኛውም ራሱን የቻለ ኩሩ ሕዝብ ሲሆኑ ራሳቸውን "ኦርማ " ብለው ይጠራሉ . ግለሰቦቻቸውን "ኢልም ኦርማ " ብለው ይጠሩታል (ከዐረብኛው "ኢብን ኤል ናስ " ጋር ይዛመድ ይሆን ) ቅዋንቅዋቸዎን ደግሞ "አፋን ኦርማ " ብለው ይጠሩታል . (Philological Society (Great Britain)., Philological Society (Great Britain), Louis Loewe 1846)

ኦርማ የሚለውን ቃል ሳጣራ ደቡብ ምሥራቅ ኬንያ ጣና ወንዝ አካባቢ የሚገኝ ጎሣ አገኘው . የኦሮሞ መነሻው መሆን አለበት ( አባ ጦቢያ ).

3. ጋሎች ከጊኒዬ መጥተው የሚቀጥሉትን የአቢሲኒያ ግዛቶች ይወራሉ , ያስገብራሉ .
ግድማ , አንጎታ , ዳውራ , ፈጣገር , ወይድ , ኢፋር , ጉራጌ , ጋንዝ , ኮንት , ዳሞታ , ዋልቃ , ቢዛማ , ሸዋ እና ባሊ
(Ancient and Modern History and Geography, Jean B. D Audiffret, 1694).

እነዚህ ከላይ የተጠቀሱትን ሥፍራዎች ጥንታዊ ካርታ ላይ ፈልገው (ኢንተርኔት ) ያግኙና ይሁኑ ካርታ ላይ ያስቀምጡ .

ስለ ኦጋዴን ደሞ እናውራ

ኦጋዴን ብዙም ሰው ብዙም ትላልቅ ከተማዎች የሌሉባት ስትሆን በ 16ኛው ክ /ዘመን ነዎሪ የነበሩትን ጋሎች የገፈተሩ ከብት አርቢር ዘላን ሶማሊኛ ተናጋሮዎች ይኖሩባታል .(Encyclopedia Britannica).

ስለ አምሐራ (አማራ ) እናውጋ

አንጡራው አምሐራ በአምሐራ ስም የሚጠራው ተራራውማና ደቡብ ምሥራቅ የሚገኘው ክ /ሀገር ነው .
እዚህ ግዛት መሐል ጥንታዊው የዘውዱ ዋና ከተማና የአቢሲኒያ የሥልጣኔ ማእከል የነበረችው ተጉለት ትገኛለች . በአሁኑ ስዓት አረመኔ በሆኑትር ድፍን ደቡብ ሐበሻን በወረሩት በአረሜነዎቹ በጋሎች ሥር ትገኛለች . (Researches into the physical history of mankind, Volume 2, James Cowles Prichard, 1837).

አሁን ደግሞ ቴዎድሮስ የኢትዮጵያውን ዘማቻ ሊጀምር ሲል ለውዳጁ ለፕላውዴን የተናገረውን እናዳምጥ

በመጀመሪያ የክርስቲያኑን መሬት የነጠቁትን , ቤት ክርስቲያንን ያወደሙትን , ነባር ነዋሪውን በግድ ያሰለሙትን ጋሎች አንክቼ እጥላለሁኝ . ለጥቆ , እስላም ወይ ይጠመቃል , ወይ አገር ለቆ ይወጣል (Travels in Abyssinia and the Galla Country. An account of a mission to Ras Ali in 1848, from the Mss of the late Waltee Chichele Plowden, her Britannic consul in Abyssinia, edited by his brother Teevoe Chichele Plowden. London, Longmans, Geen, and Co. 1868).

ቴዎድሮስና ምኒልክ ቱርክና ጋላ እየተፈራረቁ በጉልበት የነጠቅዋቸውን መሬት ባለው ሁሉ ተጠቅመው ቢያስመልሱ እነ ወያኔ , እነ ኢሕአድግ , እነ ኦነግ , እነ ኢሕአፓና መኢሶን በውሽት አንዴ ነፍጠኛ አንዴ ውራሪ እያሉ ስማቸውን አጥፍተው አጥፍተው ይኄው አሁን አንቀስ 39 ላይ ደርሰናል .

ሌላው ውሸት ጋላ የሚባለው ቃል የራሱው የጋላው ሲሆን አማራ ለሰው መናቂያ ያወጣው ነው ተብሎ ደርግ በሕግ መሻሩ ነው .

ስለዚህ ይሄንን ያነበብክ ሁሉ የቴዎድሮስ ደቀ መዝሙር የምኒልክ የደቡብ ዝመቻ ልክ ነውና አንገትህን ቀና አድርገህ አንቀስ 39ን በመጀመሪያ በሕጋዊ መንገድ ሊሠረዝ የሚችልበትን ካልሆነም አንጡራ ንብረትህን የምትጠብቅበትን አማራ ጋላ ሳትል አንድነት ፍጠር .

ሌላ ምንም ጉዳይ የለም ይሄንን ጀምረህ ሳታገባድድ .

እኔ ነኝናናናናናናናናና !

አባ ጦቢያ

Save
Cancel
Reply
 
x
OK